የስራ ላይ ልምምድ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ከሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ (Civil Rights Defenders) ጋር በመተባበር ለአዳዲስ እና ብቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሥራ ላይ ልምምድ አዘጋጅተዋል። የሥራ ላይ ልምምዱ የእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች በሀገር ውስጥ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ውስጥ በመሳተፍ ተግባራዊ ልምድ እንዲቀስሙ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በዚህ  ከ4 – 5 ወራት በሚቆየው መርሃ ግብር ተሳታፊዎች በሳምንት ለ20 ሰዓታት የሚያገለግሉ ሲሆን መጠነኛ ክፍያም ተዘጋጅቷል።

ተሳታፊዎቹ በዘርፉ የረዥም ግዜ ልምድ ካካበቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋር በመተጋገዝ ሀገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በሚያደርጉት ጥረት ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተዘጋጀው ቦታ ውስን ሲሆን፤ በጥንቃቄ የተመረጡ ከፍተኛ ብቃት ያላቸው አመልካቾች ብቻ ለውድድር ይቀርባሉ።

የመርሃ ግብሩ ቆይታ እና መጀመሪያ

መርሃ ግብሩ ከ4 እስከ 5 ወራት የሚቆይ ሲሆን እ.አ.አ ኦገስት 1 ቀን 2019 ይጀመራል።

የመርሃ ግብሩ ዓላማ

መርሃ ግብሩ 2 ግቦች አሉት፤

  1. ተሳታፊዎች በወቅታዊ የሃገራችን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እና አከባበር ሁኔታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል እና የሚሰሩበትን ተቋም የስራ ዘርፍ በሚገባ እንዲረዱት ለማስቻል፤
  2. አስተናጋጅ ድርጅቶች በአዳዲስ እና ወጣት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲጠናከሩ ለማድረግ ነው።

የተሳታፊዎች ኃላፊነት

  • በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን ማካሔድ
  • ትንታኔያዊ ዘገባዎችን ማዘጋጀት
  • የአስተናጋጅ ተቋማቱ የዕለት ተዕለት ተግባራትን ይደግፋሉ
  • በአስተናጋጅ ድርጅቶቻቸው በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ላይ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ
  • ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናሉ።

የምርጫ መስፈርት

በዚህ መርሃ ግብር የተዘጋጀው ቦታ ውስን በመሆኑ ጥቂት አመልካቾች ብቻ ለመጨረሻው ዙር ውድድር ይቀርባሉ። አመልካቾች በሚያመለክቱበት ግዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ለመስራት ጠንካራ ፍላጐት
  2. ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ
  3. በሰብዓዊ መብት ስራዎች ላይ የቀደመ ልምድ ያላቸው አመልካቾች ይበረታታሉ
  4. የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ክህሎት አስፈላጊ ሲሆን ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ክህሎት ያላቸው አመልካቾች ይበረታታሉ።

አመልካቾች

አመልካቾች ግለ ታሪካቸውን እና የሽፋን ደብዳቤያቸውን በዚህ የኢሜይል አድራሻ መላክ ይችላሉ

Email ehrproj@gmail.com

ማመለከቻ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ሐምሌ 21፤ 2011

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*