OPEN በወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ላይ ከኢሰመጉ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም)

በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም. ገዢው ፓርቲ የአመራር ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ዶ/ር ዐብይ አህመድ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መስዋዕትነት ለከፈሉ ዜጐች ያላቸውን ክብር መግለፃቸውና ስለደረሰባቸውም እንግልት ይቅርታ መጠየቃቸው፤ ዴሞክራሲ ለሀገሪቱ የህልውና ጉዳይ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ፣ የመደራጀት …