99ኛ ልዩ መግለጫ – በተያዙ ሰዎች ላይ የሚፈፀመው ሰቆቃ ይቁም

“ኢትዮጵያ የተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 5  ማንም ሰው ላይ ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ወይም ክብርን በሚያዋርድ አያያዝ መያዝ አይገባውም፤ በዚህ ሁኔታ አይቀጣም ይላል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችውና ፍፁም አስገዳጅ የሆነው የሲቪልና የፖሊቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ  ቃልኪዳንም በአንቀፅ 7 ላይ ይህንኑ መብት  ያረጋገጠና ይህ መብት በማናቸውም ሁኔታ የማይገሰስ መሆኑን በአንቀጽ 4(2) ሥር ይደነግጋል። የኤፌዲሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ18(1)ሥር ማንኛውም  ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፤ ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ  የመጠበቅ መብት እንዳለው ይደነግጋል።
ይሁን እንጂ ይህንን ህገ መንግሥታዊና ዓለም አቀፍ ሥምምነት ድንጋጌ በመተላለፍ በአቶ ፀጋዬ አየለ ግዛው ላይ ማሰቃየትና ድብደባ ከተፈፀመባቸው በኋላ በእሥር ላይ ሆነው ህክምና በመከታተል ላይ እያሉ ሕይወታቸው አልፏል።

ዝርዝሩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*