OPEN በአዲስ አበባ ለተፈፀመው ጅምላ እሥራት መንግስት በቂ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል – መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም

መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተካሔደው ጅምላ እስር ከመንግስት ሙሉ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫ ባለፈው ሳምንት በመዲናችን በተካሔደው የጅምላ እስር በከተማዋ በነበረው (ሁከት) ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል ያላቸውን 1,204 ዜጉችን ጨምሮ፤ ከጫት ቤት፣ ከሺሻ ቤትና ከቁማር ቤት በገፍ ያፈሳቸውን በአጠቃላይ ወደ ሶስት …

OPEN በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ብሔር-ተኮር ግጭቶችን እና በቡድን የተደረጁ ኃይሎች እየፈፀሟቸው ያሉትን ከባድ ጥቃቶች መንግስት በአስቸኳይ ሊያስቆም ይገባል።

መስከ ረም 8 ቀን 2011 ዓ .ም የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ ሀገሪቱ በሁለት ተጻራሪ ሁነቶች ውስጥ እያለፈች ትገኛለች። በአንድ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዷቸው መልካም ርምጃዎች ሀገሪቱ ተጋርጦባት የነበረውን ከፍተኛ ስጋት ለጊዜውም ቢሆን ያስታገሰ፣ የዜጐች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ያበረታታ፣ እንዲሁም የዲሞክራሲን ጭላንጭል የፈነጠቀ ነው። በአን …

OPEN በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና በድሬደዋ ከተማ ከቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በተፈፀመ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ – ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓም

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ውስጥ ከቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በተፈፀመ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃትና ስርዓት አልበኝነት በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተፈፅሟል። በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ዜጐች ተገድለዋል፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ተዘርፈዋል፣ በርካታ ንብረትም ወድሟል፤ በጅግጅጋ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አብያተ-ክርስትያናት በእሳት ተቃጥለዋል፡፡ በተደራጁ ወጣቶች የሚ …

OPEN 144ኛ ልዩ መግለጫ – በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ሰብአዊ መብትች ጉባኤ ልዩ መግለጫውን ይፋ አድርጓል። በሰብአዊ መብቶች ጉባኤ 144ኛ ልዩ መግለጫ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የተፈጸሙት ከጥር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2010 ዓ.ም ባሉት 12ወራት ሲሆን ሪፖርቱ በዜጎች ላይ የተፈፀመ ግድያን፣ …

OPEN በግብር ጭማሪው ላይ ቅሬታና ተቃውሞ ለሚያሰሙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የሚሰጠው መንግሥታዊ ምላሽና የጉዳዩ አያያዝ ሰብዓዊና የዜግነት መብቶቻቸውን የጠበቀ ሊሆን ይገባል፤ በክልሎች መካከል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችም በአስቸኳይ እልባት ይሰጣቸው

  የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ በግብር ጭማሪው ላይ ከንግዱ ማህበረሠብ ለተነሳው ቅሬታና ተቃውሞ እንዲሁም በክልሎች መካከል ለሚነሱት ግጭቶች ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠየቀ። ሰመጉ ጳጉሜ 04 ቀን 2009 ዓም ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ‹‹አማካይ የቀን ገቢ ግምት›› በማለት በንግድ ማህበረሰቡ ላይ የጣለውን የግብር መጠን ተከትሎ ከንግድ ማህበረሰቡ የገቢ ግም …