OPEN ሰመጉ በመንግስት የታገደበት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዲለቀቅለት ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤትን በደብዳቤ ጠየቀ።

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ከህግ አግባብ ውጭ በ2002 ዓ.ም በኢፌድሪ በጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ በተፃፈ ደብዳቤ የታገደበትን ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺ አንድ መቶ ሰማንያ አራት ብር እንዲለቀቅለት ለጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ ቤት ደብዳቤ አስገባ። ለጠቅላየ ሚንስቴር ፅ/ቤት የተፃፈ ደብዳቤ በፒዲኤፍ  

OPEN 144ኛ ልዩ መግለጫ – በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ሰብአዊ መብትች ጉባኤ ልዩ መግለጫውን ይፋ አድርጓል። በሰብአዊ መብቶች ጉባኤ 144ኛ ልዩ መግለጫ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የተፈጸሙት ከጥር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2010 ዓ.ም ባሉት 12ወራት ሲሆን ሪፖርቱ በዜጎች ላይ የተፈፀመ ግድያን፣ …

OPEN “በኢትዮጵያ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተወሠደ የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋ::” ሂውማን ራይትስ ዎች

ሂውማን ራይትስ ዎች ሰኔ 9 ቀን 008 ዓ ም ባወጣው ባለ 61 ገጽ ሪፖርት ” `ጭካኔ የተሞላበት አፈና`_የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ” የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በወሰደው ከመጠን ያለፈ የሃይል ርምጃ ከ400 በላይ የሚሆኑ ዜጐች መገደላቸውን፣ ከአስር ሺህ በላይ መታሰራቸውን፣ ሌሎች የመብት ጥሰቶችም መፈጸማቸውን ገልጿል።