OPEN የራያ እና የወልቃይት የማንነት እና እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን አስመልክቶ ከሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በትግራይ ክልል አላማጣ ከተማ የራያን ህዝብ የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ይዘው ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓም ሰልፍ በወጡ ዜጐች ላይ የክልሉ ልዩ ኃይል በወሰደው የሃይል እርምጃ ቢያንስ 9 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸውን፤ 16 ወጣቶች በጥይት መቁሰላቸውን፤ እንዲሁም ከ50 በላይ ወጣቶች እየተደበደቡ ታፍነው መወሰዳቸውን ምንጮች ለሰመጉ አረጋግጠዋል …

OPEN በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በአጎራባች አካባቢዎች እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁም! ለብሔር ተኮር ጥቃቶች እና ግጭቶች ሕጋዊና ፖለቲካዊ መፍትሔ ይሰጣቸው!!

መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ከዚህ ቀደም በቤኒሻንጉልና ኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ያስከተሉትን ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የንብረት ውድመት በአካባቢው በመገኘት በባለሙያዎቹ አማካኝነት በማጣራት የደረሠውን የጉዳት መጠን እና ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች ይፋ አድርጓል፡፡ ለትውስታ ያህል ሐምሌ 10 ቀን 2000 ዓ.ም የሰብ …

OPEN በአዲስ አበባ ለተፈፀመው ጅምላ እሥራት መንግስት በቂ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል – መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም

መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተካሔደው ጅምላ እስር ከመንግስት ሙሉ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫ ባለፈው ሳምንት በመዲናችን በተካሔደው የጅምላ እስር በከተማዋ በነበረው (ሁከት) ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል ያላቸውን 1,204 ዜጉችን ጨምሮ፤ ከጫት ቤት፣ ከሺሻ ቤትና ከቁማር ቤት በገፍ ያፈሳቸውን በአጠቃላይ ወደ ሶስት …

OPEN በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ብሔር-ተኮር ግጭቶችን እና በቡድን የተደረጁ ኃይሎች እየፈፀሟቸው ያሉትን ከባድ ጥቃቶች መንግስት በአስቸኳይ ሊያስቆም ይገባል።

መስከ ረም 8 ቀን 2011 ዓ .ም የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ ሀገሪቱ በሁለት ተጻራሪ ሁነቶች ውስጥ እያለፈች ትገኛለች። በአንድ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዷቸው መልካም ርምጃዎች ሀገሪቱ ተጋርጦባት የነበረውን ከፍተኛ ስጋት ለጊዜውም ቢሆን ያስታገሰ፣ የዜጐች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ያበረታታ፣ እንዲሁም የዲሞክራሲን ጭላንጭል የፈነጠቀ ነው። በአን …

OPEN 145ኛ ልዩ መግለጫ – በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ እና አካባቢው የተፈፀመ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት – ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ.ም

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በ145ኛ ልዩ መግለጫ የተመለከተው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ሲሆን የመብት ጥሰቱ የተፈጸመው ከሕዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 04 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ነው።  ሰመጉ ባለሙያዎቹን ወደ አካባቢው ልኮ የማጣራት ሥራውን የሰራው ከየካቲት 05 እስከ የካቲት 12 ቀን 2 …

OPEN በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና በድሬደዋ ከተማ ከቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በተፈፀመ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ – ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓም

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ውስጥ ከቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በተፈፀመ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃትና ስርዓት አልበኝነት በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተፈፅሟል። በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ዜጐች ተገድለዋል፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ተዘርፈዋል፣ በርካታ ንብረትም ወድሟል፤ በጅግጅጋ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አብያተ-ክርስትያናት በእሳት ተቃጥለዋል፡፡ በተደራጁ ወጣቶች የሚ …