Latest Posts

የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት ይከበር!! በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚወሰድ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም!!

የህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲከበርና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ሰመጉ ጠየቀ። ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ ም ሰመጉ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መንግስት የሚያደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሐገሪቱን ወደ ከባድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ እናዳያስገባት ስጋቱን ገልጿል።

ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀመሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተባብሶ የቀጠለው ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ በርካታ ዜጐችን ለሞትና ለአካል ጉድለት ሲዳርግ፤ በሃገራችን ያለው የሰብዓዊ መብቶች አያያዝም ከመቼውም በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይም በህገ መንግስቱ የተረጋገጡትን የዜጐች የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ለመግታት በመንግስት እየተወሰደ ያለው የኃይል ርምጃ የዜጐችን ህይወት ከመቅጠፍና አካል ማጉደል አልፎ የሐገሪቱን ሰላምና ጸጥታ አስጊ ደረጃ ላይ ጥሎታል።

በተለያዩ የሐገራችን ክልሎች በተለይም በሰሜንና ደቡበ ጐንደር፤ በባህርዳር፤ በምዕራብና ምስራቅ ጐጃም የተቀጣጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ግጭት ተሸጋግሮ በርካታ ዜጐች ለሞት ተዳርገዋል። በተለይም በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 ልዩ ስሙ “ዓባይ ማዶ” አካባቢ ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ከ50 በላይ ዜጐች የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥይት ሰለባ መሆናቸውን ሰመጉ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

በተያያዘም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዳግም ያገረሸው ህዝባዊ ተቃውሞ ተስፋፍቶ በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፤ በምስራቅና በምዕራብ ሐረርጌ፤ በጅማ፤ በዝዋይ፤ በአርሲ፤ በሻሸመኔና በሌሎችም ከተሞች በመዳረስ ላይ ይገኛል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያግኙ፡

ብሄር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም!

ሙሉ መግለጫውን ከዚህ በታች ያንብቡ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ አሎ ቀበሌ የተፈፀመ የመብት ጥሰት የመብት ጥሰቱ የኋላ ታሪክ

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮች የተለያዩ አይነት ሰብሎችን በመዝራት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን ክልሉንና በአጠቃላይም ለሀገሪቱ ገበያ የሚቀርብ ምርት በማምረት የሚታወቁ ውጤታማ አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ ይሁንና በአካባቢው የሚገኙ ባለስልጣናትና የጸጥታ ሀላፊዎች እነዚህን አርሶ አደሮች “እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጅ ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው… ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፣ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ” በማለት ንብረታቸውን በተለያየ ጊዚ በመንጠቅ እነዚህንም አርሶ አደሮች በተለያዩ ጊዜያት ለህገወጥ እስራት ዳርገዋቸዋል፡፡ የአካባቢውን ተወላጅ ህዝብም “በናንተ መሬት ነው ሀብት ያፈሩት …” እያሉ ጥላቻንና ግጭትን ሲሰእኩ ቆይተዋል፡፡

በተለይም መጋቢት 27 2007 ዓ.ም አቶ ዘመዱ እንዳለ የተባለ የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ ተገድሎ ይገኛል፡፡ እዚህ ላይ ለጊዜው ስሙን የማንገልጸው የግድያ ድርጊቱ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ጉዳዩ ውሳኔ ሣያገኝ፣ ይህ “ግድያ የተፈፀመው በአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ነው“ በማለት የኖኖ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር ሀይሉ ድሪባ፣ የናኖ አሎ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጎሳዬ ገች እና መቶ አለቃ ገነነ በየነ የተባሉ የፖሊስ አባላት የቀበሌ አመራሮችንና የፖሊስ አባላትን በማስተባበር የአካባቢው ህዝብ በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ እንዲነሳ በማነሳሳት ሚያዝያ 9 2007 ዓ.ም 85 አርሶ አደር አባወራዎችን ለእስራት ከዳረጉዋቸው በኋላ ቅዳሜ ማለትም ሚያዝያ 10 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት አካባቢ ዘር በመምረጥ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች መኖሪያ ቤትና ንብረት ነው ያሉትን እየመረጡ በእሳት እንዳቃጠሉ የታሰሩትንም አባወራዎች ከእያንዳንዳቸው 300 ብር ለነዳጅ ብለው ከተቀበሉዋቸው በኋላ ቤታችሁ ተቃጥሏል፣ ሂዱ በማለት ከእስር እንደለቀቁዋቸው ለሰመጉ በቀረበ ማመልከቻና የሰመጉ ባለሙያዎችም በአካባቢው ለማጣራት በሄዱበት ወቅት ያነጋገሩዋቸው ቤት ንብረት የተቃጠለባቸው አርሶ አደሮች አስረድተዋል፡፡ የሰመጉ ባለሙያዎች ከኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ ጋር ሁት ጊዜ በስልክ ግንኙነት አድርገዋል፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ በዚህ መግለጫ ውስጥ የተጠቀሱት ቤቶች ከነሙሉ ንብረታቸውን ቤቶቹ በተቃጠሉበት ቦታ ላይ 24 የቆርቆሮ ሥራ መጀመሩን፣ ቤት ለተቃጠለባቸው እና ንብረት ለወደመባቸው ዜጎች የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት በራስ ተነሳሽነት ገንዘብና እህል አዋጥተው ለተጎጂዎች እርዳታ እንዲደርሳቸው እየተደረገ መሆኑንና ተጎጂዎቹ ተረጋግተው እንዲኖሩ ለማድረግ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑን አተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የአካባቢው ሕዝብ በራሱ ተነሳሽነት የዕርዳታ ገንዘብና እህል ማዋጣቱ ቢረጋገጥም እርዳታው ግን ይህ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ደረስ ለተጎጂዎቹ አለመድረሱን ሰመጉ አረጋግጧል፡፡

የደረሰ የንብረትና የህይወት ጉዳት በቁጥር                

  • የ1 ሰው ህይወት አልፏል
  • 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል
  • 99 የሳር ክዳን ቤቶች በእሳት ተቃጥለው ወድመዋል
  • 25 የቆርቆሮ ክዳን መኖሪያ ቤቶች በእሳት ተቃጥለው ወድመዋል

የአርሶ አደሮቹን መኖሪያቤትና ንብረት ቃጠሎ ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች፣ ህፃናትና አቅመደካሞች የሚገኙባቸው ተፈናቃዮች ከአካባቢያቸው በመሰደድ ወደ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ሀበሸጌ ወረዳ ድንኳን ውስጥ ተጠልለው ሲረዱ ቆይተዋል፡፡

 

 damena gizaw
 ፎቶ ግራፍ 1፡ ሟች አቶ ዳመና ግዛው ሚያዝያ 10 2007 ዓ.ም በፖሊስ ኩላሊታቸው ላይ ተረግጠው ህይወታቸው ያለፈ የቀብር ስነስርአታቸውም በ11/08/2007 ዓ.ም በዳርጌ ማርያም ተፈፅሟል፡፡

ሙሉ መግለጫውን ከዚህ በታች ያንብቡ

 

መንግሥት ለዜጎች ሕይወት፣ አካል፣ ንብረትና ነጻነት በቂ ጥበቃ ያድርግ!! 

ዓርብ ሚያዝያ ሰባት ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በኢትጵያ ጋማቤላ ክልል ኑዌር ዞን ሦስት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 13 ቀበሌዎች ውስጥ ‹‹ከደቡብ ሱዳን የመጡ››

 

በመንግሥት የጸጥታና ታጣቂ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚፈጸም አሠቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁሙ

Oromo  mothers mourning

በመንግሥት የጸጥታና ታጣቂ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚፈጸም አሠቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁሙ!

ሰመጉ በ140ኛ ልዩ መግለጫው በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አጋልጧል፡፡ ሙሉ መግለጫውን ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡

 

መልዕክተ ሰመጉ ሰኔ 2008

june2008 newsletter image

መልዕክተ ሰመጉ ሰኔ 2008 

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ወርኃዊ ልሣን የሆነችውን መልዕክተ ሰመጉ የሰኔ ወር ዕትም ከዚህ በታች ይመልከቱ

መልዕክተ ሰመጉ

በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጐችን ከቤት ንብረት የማፈናቀል ድርጊት ይቁም!!

HRCO’s Press Release, House Demolishing July 1 2016

በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጐችን ከቤት ንብረት የማፈናቀል ድርጊት ይቁም!!

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የከተማው አስተዳደር ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር አይጣጣምም በሚል ምክንያት በርካታ ቤቶችን በማፍረስ ላይ ይገኛል። በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጐችም ለከፍተኛ አደጋም ተጋልጠው ይገኛሉ። በተለይ ቤት ማፍረሱ በክረምት ወቅት መሆኑ የጉዳቱን መጠን የከፋ አድርጐታል።   ሰመጉ ይህንን መግለጫ እስካወጣበት ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ ም ድረስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በአፍራሽ ግብረ ኃይል እንዲፈርሱ ተደርገዋል።

የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ የጫኑ

HRCO’s Press Release, House Demolishing July 1 2016