Latest Posts

በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጐችን ከቤት ንብረት የማፈናቀል ድርጊት ይቁም!!

HRCO’s Press Release, House Demolishing July 1 2016

በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጐችን ከቤት ንብረት የማፈናቀል ድርጊት ይቁም!!

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የከተማው አስተዳደር ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር አይጣጣምም በሚል ምክንያት በርካታ ቤቶችን በማፍረስ ላይ ይገኛል። በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጐችም ለከፍተኛ አደጋም ተጋልጠው ይገኛሉ። በተለይ ቤት ማፍረሱ በክረምት ወቅት መሆኑ የጉዳቱን መጠን የከፋ አድርጐታል።   ሰመጉ ይህንን መግለጫ እስካወጣበት ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ ም ድረስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በአፍራሽ ግብረ ኃይል እንዲፈርሱ ተደርገዋል።

የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ የጫኑ

HRCO’s Press Release, House Demolishing July 1 2016

 

“በኢትዮጵያ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተወሠደ የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋ::” ሂውማን ራይትስ ዎች

ሂውማን ራይትስ ዎች ሰኔ 9 ቀን 008 ዓ ም ባወጣው ባለ 61 ገጽ ሪፖርት ” `ጭካኔ የተሞላበት አፈና`_የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ” የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በወሰደው ከመጠን ያለፈ የሃይል ርምጃ ከ400 በላይ የሚሆኑ ዜጐች መገደላቸውን፣ ከአስር ሺህ በላይ መታሰራቸውን፣ ሌሎች የመብት ጥሰቶችም መፈጸማቸውን ገልጿል።

images

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፡ ሕገወጥ እስራት፡ አፍኖ መሠወር፡ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም

ሰመጉ 141ኛ ልዩ መግለጫውን ይፋ አደረገ።

HRCO 141st Special Report Amharic Scanned

“በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፡ ሕገወጥ እስራት፡ አፍኖ መሠወር፡ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!” በሚል ባወጣው መግለጫ የወልቃይት፡ የቅማንት፡ የቁጫና የኮንቶማ ማህበረሰቦች አባላት ያነሷቸውን የማንነት ጥያቄዎች ተከትሎ በየክልሎቹ የተነሱ ግጭቶች የደረሰውን የሰው ህይወት መጥፋት፤ የአካል መጉደል፤ ህገወጥ እስራት፤ ድብደባ፤ የንብረት ውድመትና የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶችን አጋልጧል።

HRCO 141st Special Report Amharic Scanned

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፤ ሕገወጥ እስራት፤ አፍኖ መሠወር፤ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!

ሰመጉ 141ኛ ልዩ መግለጫውን ይፋ አደረገ።

HRCO 141st Special Report Amharic (Sene 01 2008)

“በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፤ ሕገወጥ እስራት፤ አፍኖ መሠወር፤ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!” በሚል ባወጣው መግለጫ የወልቃይት፤ የቅማንት፤ የቁጫና የኮንቶማ ማህበረሰቦች አባላት ያነሷቸውን የማንነት ጥያቄዎች ተከትሎ በየክልሎቹ የተነሱ ግጭቶች የደረሰውን የሰው ህይወት መጥፋት፤ የአካል መጉደል፤ ህገወጥ እስራት፤ ድብደባ፤ የንብረት ውድመትና የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶችን አጋልጧል።

የሪፖርቱን ሙሉ ዝርዝር ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

HRCO 141st Special Report Amharic (Sene 01 2008)

 

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ሕገወጥ እስራት፣ አፍኖ መሠወር፣ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!!

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፡ ሕገወጥ እስራት፡ አፍኖ መሠወር፡ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!!” በሚል ባወጣው 141ኛ ልዩ መግለጫ የወልቃይት፡ የቅማንት፡ የቁጫና የኮንቶማ ማህበረሰቦች አባላት ያነሷቸውን የማንነት ጥያቄዎች ተከትሎ በየክልሎቹ የተነሱ ግጭቶች የደረሰውን የሰው ህይወት መጥፋት፤ የአካል መጉደል፤ ህገወጥ እስራት፤ ድብደባ፤ የንብረት ውድመትና የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶችን አጋልጧል።

ሰመጉ ባደረገው ምርመራ የወልቃይት ተወላጆች ህወሃት በትጥቅ ትግል ላይ ከነበረበት ግዜ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎችና ግዜያት “እኛ አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም” በማለት የአማራ ብሔረተኝነት የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ተቃውሟቸውን በተከታታይ በሰላማዊ መንገድ ባሰሙ የወልቃይት ማሕበረሠብ አባላት ላይ በአካባቢው የሚገኙ የትግራይ ክልል መንግሥት የፀጥታ ሃይሎች መሆናቸውን አብራርቷል።

ሰመጉ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ከወልቃይት አካባቢ በትግራይ ክልል መንግሥት የፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ 34 ሰዎች፤ ታፍነው የደረሱበት ያልታወቀ 93 ሰዎች፤ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ 137 ሰዎችን ጨምሮ ድብደባና ማሠቃየት የደረሰባቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ማግኘት ችሏል። በተመሳሳይም የቅማንት ማሕበረሰብን የብሔረሰብን የማንነት ጥያቄ ተከትሎ የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጥቅምት 22 2008  ዓም በአርማጭሆ ወረዳ፤ ማውራ ቀበሌ ውስጥ በወሰዱት የኃይል እርምጃ በህገወጥ መንገድ የተገደሉ 22 ሰዎች ዝርዝር ለማጣራት ተችሏል።

105ኛ ልዩ መግለጫ- ሕጋዊ መፍ ት ሔ የሚሻ ሕገ ወጥ ድርጊት

“በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በጋሞጎፋ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በወላይታ እና በኦቾሎ ብሄረሰብ አባላት መካከል በ1992 ዓ.ም  በይዞታ ይገባኛል ሰበብ በተፈጠረ ግጭት በወላይታ ተወላጆች ላይ የሕይወት መጥፋት ፣ የንብረት መወደም  እና የወላይታ ብሄረሰብ ተወላጆች ከእድር እንደማስወጣት ያሉ የተለያዩ የማሕበራዊ ሕይወት ችግሮች ደርሰው ነበር።

ይህን ተከትሎ ከእድር እንዲወጡ የተደረጉት የወላይታ ብሄረሰብ ተወላጆች ከሌሎች ብሄረሰብ አባላት ጋር በመኾን አዲስ እድር በማቋቋም እየተረዳዱ የቆዩ ሲሆን ታህሳስ 3, 1999 ዓ.ም በላንቴ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ውስጥ በኦቾሎ ብሄረሰብ እድር ውጭ ሌላ እድር ሊኖር ስለማይገባ በአስቸኳይ እንድታፈርሱ የሚል ትእዛዝ ከላንቴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሊቀመንብር ከአቶ አለማየሁ አሻ እና ከኦቾሎ ባህል አስፈጻሚዎች ለእድሩ አመራር ኮሚቴዎች ትእዛዝ ማስተላለፉን እና ለማፍረስ ፈቃደኛ ባለመኾናቸው ምክን ያት በተለያዩ ጊዜያት የእድሩን መገልገያ እቃዎች ለመውሰድ ሙከራዎች መደረጋቸውን እና ይህንንም ህገ ወጥ ድርጊት በወቅቱ  ከወረዳ እስከ ዞን አስተዳደር ድረስ ቢያሳውቁም መፍት ሄ ሊያገኙ አልቻሉም።”
ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ