OPEN የራያ እና የወልቃይት የማንነት እና እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን አስመልክቶ ከሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በትግራይ ክልል አላማጣ ከተማ የራያን ህዝብ የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ይዘው ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓም ሰልፍ በወጡ ዜጐች ላይ የክልሉ ልዩ ኃይል በወሰደው የሃይል እርምጃ ቢያንስ 9 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸውን፤ 16 ወጣቶች በጥይት መቁሰላቸውን፤ እንዲሁም ከ50 በላይ ወጣቶች እየተደበደቡ ታፍነው መወሰዳቸውን ምንጮች ለሰመጉ አረጋግጠዋል …