OPEN ሰመጉ በመንግስት የታገደበት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዲለቀቅለት ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤትን በደብዳቤ ጠየቀ።

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ከህግ አግባብ ውጭ በ2002 ዓ.ም በኢፌድሪ በጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ በተፃፈ ደብዳቤ የታገደበትን ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺ አንድ መቶ ሰማንያ አራት ብር እንዲለቀቅለት ለጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ ቤት ደብዳቤ አስገባ። ለጠቅላየ ሚንስቴር ፅ/ቤት የተፃፈ ደብዳቤ በፒዲኤፍ  

OPEN የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፃሚዎች ላይ መንግስት በመውሰድ ላይ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል!!

ሕዳር 04 ቀን 2011 ዓ.ም. የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰኞ ሕዳር 03 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ አሰቃቂ ድርጊት የሚፈጸምባቸው 7 ድብቅ እስር ቤቶች መገኘታቸውን፤ ከእነዚህም በተጨማሪ በማረሚያ ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎችም ጭምር በተጠረጣሪዎች ላይ ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ እጅግ አሰቃቂ ድርጊቶች ሲፈፀሙ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ከእነዚህ በህግ ጥላ ስር በ …