የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) መንግስት ለብሔረሰብ ተኮር ጥቃቶች የማያዳግም የፖሊሲና የአፈፃፀም መፍትሔ እንዲሰጥ ጠየቀ። ሰመጉ በ143ኛ ልዩ መግለጫው በኢትዮጵያ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እና ግጭቶች እጅጉን ተባብሰው መቀጠላቸውንና አሳሳቢ ቀውስና መዘዝ በማስከተል ላይ መሆናቸውን ገልጿል። መግለጫው በጌዴኦ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የብሔረሰቡ ተወላጅ ባልሆኑ ዜጐች ላይ የተፈጸመውን ግድያ፣ ድብደባ፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ቃጠሎ በዝርዝር አካቷል። በተጨማሪም በሐረሪ ክልል የአፍረንቀሎ የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማዕከልን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ መጣልን ተከትሎ በኦሮሞ ማሕበረሰብ ወጣቶች ላይ የደረሰውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችንም ይፋ አድርጓል።
መንግስት ከብሔር ጋር ለተያያዙ ጥቃቶች እና ግጭቶች በቂ ትኩረት ባለመስጠቱ የበርካታ ዜጐች ህይወት መጥፋቱን፣ አካል መጉደሉን፣ በመቶ ሺዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ መገደዳቸውን አስታውሶ፤ ከፌዴራል እስከ ክልል ያሉ የመንግስት ባለሥልጣናት ራሳቸውን እንዲመለከቱ እና ህዝብን ከህዝብ ከሚያጋጭና ሐገርን ከሚጐዳ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሰመጉ ጠይቋል። መንግሥትም ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ሰጥቶ ዘለቄታዊ መፍትሔ እንዲፈልግለት አሳስቧል፡
ሙሉ መግለጫውን እዚህ ያግኙ