ሂውማን ራይትስ ዎች ሰኔ 9 ቀን 008 ዓ ም ባወጣው ባለ 61 ገጽ ሪፖርት ” `ጭካኔ የተሞላበት አፈና`_የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ” የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በወሰደው ከመጠን ያለፈ የሃይል ርምጃ ከ400 በላይ የሚሆኑ ዜጐች መገደላቸውን፣ ከአስር ሺህ በላይ መታሰራቸውን፣ ሌሎች የመብት ጥሰቶችም መፈጸማቸውን ገልጿል።
“በኢትዮጵያ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተወሠደ የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋ::” ሂውማን ራይትስ ዎች
