OPEN “በኢትዮጵያ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተወሠደ የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋ::” ሂውማን ራይትስ ዎች

ሂውማን ራይትስ ዎች ሰኔ 9 ቀን 008 ዓ ም ባወጣው ባለ 61 ገጽ ሪፖርት ” `ጭካኔ የተሞላበት አፈና`_የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ” የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በወሰደው ከመጠን ያለፈ የሃይል ርምጃ ከ400 በላይ የሚሆኑ ዜጐች መገደላቸውን፣ ከአስር ሺህ በላይ መታሰራቸውን፣ ሌሎች የመብት ጥሰቶችም መፈጸማቸውን ገልጿል።