100ኛ ልዩ መግለጫ- አጥፊዎች ለፍርድ መቅረባቸው በጎ ድርጊት ነው

“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)  በተለያዩ ጊዜ የተከሰቱ የጎሳ ግጭቶችን፣ እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተውን የሀይማኖት ግጭት አስመልክቶ ባወጣቸው መግለጫዎች ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ተገቢ ካስ እንዲሰጣቸው ግጭቶቹ እንዳይደገሙ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ማሳሰቡ ይታወቃል።
ኢሰመጉ በዚህ 100 ኛ መግለጫው ከላይ ለተጠቀሰው የሀይማኖት ግጭት  ተጠያቂ የሆኑት ግለሰቦ ፤ለፍርድ መቅረባቸው እንዲሁም በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ሕዝቦች ብሄራዊ ክልል መንግስት በጌዲኦ ዞን መጋቢት 28, 1998  ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በከፊልም ቢሆን የመቋቋሚያ ገንዘብ በክልሉ መንግስት መሰጠቱ በጎ እርምጃ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስድ ይጠይቃል። ”

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*