OPEN ሰመጉ 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሊያካሂድ ነው

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው የፊታችን እሑድ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ይጀመራል፡፡ በጉባዔው የ2008 – 2009 ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርት፤ የውስጥ እና የውጭ ሪፖርት የሚቀርብ ሲሆን፣ የ2009 – 2010 ዓ.ም ዕቅድና በጀት ሪፖርትም ይቀርባል፡፡ በጉባዔው ላይ …

OPEN በሐገራችን እውነተኛ ዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍንና ሰብዓዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ከምን ጊዜውም የበለጠ ጥረት ለማድረግ ቃላችንን በድጋሚ እናጸናለን!!!

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ)፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተር አንቀጽ 1(ሀ) እና በኢትዮጵያ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር ከ404-482 በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት መስከረም 29 ቀን 1984 ዓ.ም. በአባላት የተመሠረተ የመጀመሪያው መንግሥታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ነው፡፡ ሰመጉ በበጎ አድራጎትና ማኅበራት ዐዋጅ ቁጥር 621 …

OPEN የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት ይከበር!! በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚወሰድ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም!!

የህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲከበርና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ሰመጉ ጠየቀ። ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ ም ሰመጉ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መንግስት የሚያደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሐገሪቱን ወደ ከባድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ እናዳያስገባት ስጋቱን ገልጿል። ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀመሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች …

OPEN መንግሥት ለዜጎች ሕይወት፣ አካል፣ ንብረትና ነጻነት በቂ ጥበቃ ያድርግ!! 

ዓርብ ሚያዝያ ሰባት ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በኢትጵያ ጋማቤላ ክልል ኑዌር ዞን ሦስት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 13 ቀበሌዎች ውስጥ ‹‹ከደቡብ ሱዳን የመጡ››  

OPEN በመንግሥት የጸጥታና ታጣቂ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚፈጸም አሠቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁሙ

በመንግሥት የጸጥታና ታጣቂ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚፈጸም አሠቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁሙ! ሰመጉ በ140ኛ ልዩ መግለጫው በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አጋልጧል፡፡ ሙሉ መግለጫውን ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡