OPEN ሰመጉ 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

ሰመጉ 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. አካሄደ፡፡ ጉባዔው በሰመጉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብጽዓተ ተረፈ ‹‹የእንኳን ደህና መጣችሁ›› መልዕክት የተከፈተ ሲሆን፣ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የድርጅቱ መሥራችና አንጋፋ አባላት የምስጋናና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ በተያያዘም፣ ዋና ዳይሬክተሩ ለሰመጉ መሥራች አባት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያም ከድርጅ

OPEN ሰመጉ 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሊያካሂድ ነው

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው የፊታችን እሑድ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ይጀመራል፡፡ በጉባዔው የ2008 – 2009 ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርት፤ የውስጥ እና የውጭ ሪፖርት የሚቀርብ ሲሆን፣ የ2009 – 2010 ዓ.ም ዕቅድና በጀት ሪፖርትም ይቀርባል፡፡ በጉባዔው ላይ

OPEN ሰመጉን ይደግፉ ለሰብዓዊ መብች መከበር የበኩልዎን አስተዋጽዖ ያበርክቱ

hrco-fund-raising-events-20 ሰመጉን ይደግፉ ለሰብዓዊ መብች መከበር የበኩልዎን አስተዋጽዖ ያበርክቱ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) በኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተር አንቀጽ 1(ሀ) እና በኢትዮጵያ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር ከ404–482 በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት መስከረም 29 ቀን 1984 ዓ.ም. በአባላት የተመሠረተ ማኅበር ነው፡፡ ሰመጉ በበጎ አድራጎትና ማኅበራት ዐዋጅ ቁጥር

OPEN የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት ይከበር!! በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚወሰድ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም!!

የህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲከበርና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ሰመጉ ጠየቀ። ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ ም ሰመጉ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መንግስት የሚያደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሐገሪቱን ወደ ከባድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ እናዳያስገባት ስጋቱን ገልጿል። ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀመሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች

OPEN ብሄር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም!

ሙሉ መግለጫውን ከዚህ በታች ያንብቡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ አሎ ቀበሌ የተፈፀመ የመብት ጥሰት የመብት ጥሰቱ የኋላ ታሪክ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮች የተለያዩ አይነት ሰብሎችን በመዝራት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን ክልሉንና በአጠቃላይም ለሀገሪቱ ገበያ የሚቀርብ ምርት በማምረት የሚታ