በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ሕገወጥ እስራት፣ አፍኖ መሠወር፣ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!!

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያ፡ ሕገወጥ እስራት፡ አፍኖ መሠወር፡ ማፈናቀልና ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም!!” በሚል ባወጣው 141ኛ ልዩ መግለጫ የወልቃይት፡ የቅማንት፡ የቁጫና የኮንቶማ ማህበረሰቦች አባላት ያነሷቸውን የማንነት ጥያቄዎች ተከትሎ በየክልሎቹ የተነሱ ግጭቶች የደረሰውን የሰው ህይወት መጥፋት፤ የአካል መጉደል፤ ህገወጥ እስራት፤ ድብደባ፤ የንብረት ውድመትና የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶችን አጋልጧል።

ሰመጉ ባደረገው ምርመራ የወልቃይት ተወላጆች ህወሃት በትጥቅ ትግል ላይ ከነበረበት ግዜ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎችና ግዜያት “እኛ አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም” በማለት የአማራ ብሔረተኝነት የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ተቃውሟቸውን በተከታታይ በሰላማዊ መንገድ ባሰሙ የወልቃይት ማሕበረሠብ አባላት ላይ በአካባቢው የሚገኙ የትግራይ ክልል መንግሥት የፀጥታ ሃይሎች መሆናቸውን አብራርቷል።

ሰመጉ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ከወልቃይት አካባቢ በትግራይ ክልል መንግሥት የፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ 34 ሰዎች፤ ታፍነው የደረሱበት ያልታወቀ 93 ሰዎች፤ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ 137 ሰዎችን ጨምሮ ድብደባና ማሠቃየት የደረሰባቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ማግኘት ችሏል። በተመሳሳይም የቅማንት ማሕበረሰብን የብሔረሰብን የማንነት ጥያቄ ተከትሎ የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጥቅምት 22 2008  ዓም በአርማጭሆ ወረዳ፤ ማውራ ቀበሌ ውስጥ በወሰዱት የኃይል እርምጃ በህገወጥ መንገድ የተገደሉ 22 ሰዎች ዝርዝር ለማጣራት ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*