Latest Posts

100ኛ ልዩ መግለጫ- አጥፊዎች ለፍርድ መቅረባቸው በጎ አድርጊት ነው

“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ የጎሳ ግጭቶችን፣ እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተውን የሀይማኖት ግት አስመልክቶ ባወጣቸው መግለጫዎች ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ተገቢ ካሳ እንዲሰጣቸውና ፣ ግጭቶቹ እንዳይደገሙ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈግላቸው ማሳሳቡ ይታወቃል።

ኢሰመጉ በዚህ 100ኛ መግለጫው ከላይ ለተጠቀሰው የሀይማኖት ግጭት ተጠያቂ የሆኑት ግለሰቦች ለፍርድ በመቅረባቸው እንዲሁም በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጌዲኦ ዞን መጋቢት 28 ቀን 1999 ዓ.ም ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በከፊልም ቢሆን የማቋቋሚያ ገንዘብ በክልሉ መንግሥት በጎ እርምጃ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ተጨማሪ  እርምጃዎችን እንዲወስድ ይጠይቃል።”

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

99ኛ ልዩ መግለጫ – በተያዙ ሰዎች ላይ የሚፈፀመው ሰቆቃ ይቁም

“ኢትዮጵያ የተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 5  ማንም ሰው ላይ ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ወይም ክብርን በሚያዋርድ አያያዝ መያዝ አይገባውም፤ በዚህ ሁኔታ አይቀጣም ይላል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችውና ፍፁም አስገዳጅ የሆነው የሲቪልና የፖሊቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ  ቃልኪዳንም በአንቀፅ 7 ላይ ይህንኑ መብት  ያረጋገጠና ይህ መብት በማናቸውም ሁኔታ የማይገሰስ መሆኑን በአንቀጽ 4(2) ሥር ይደነግጋል። የኤፌዲሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ18(1)ሥር ማንኛውም  ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፤ ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ  የመጠበቅ መብት እንዳለው ይደነግጋል።
ይሁን እንጂ ይህንን ህገ መንግሥታዊና ዓለም አቀፍ ሥምምነት ድንጋጌ በመተላለፍ በአቶ ፀጋዬ አየለ ግዛው ላይ ማሰቃየትና ድብደባ ከተፈፀመባቸው በኋላ በእሥር ላይ ሆነው ህክምና በመከታተል ላይ እያሉ ሕይወታቸው አልፏል።

ዝርዝሩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

100ኛ ልዩ መግለጫ- አጥፊዎች ለፍርድ መቅረባቸው በጎ ድርጊት ነው

“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)  በተለያዩ ጊዜ የተከሰቱ የጎሳ ግጭቶችን፣ እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተውን የሀይማኖት ግጭት አስመልክቶ ባወጣቸው መግለጫዎች ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ተገቢ ካስ እንዲሰጣቸው ግጭቶቹ እንዳይደገሙ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ማሳሰቡ ይታወቃል።
ኢሰመጉ በዚህ 100 ኛ መግለጫው ከላይ ለተጠቀሰው የሀይማኖት ግጭት  ተጠያቂ የሆኑት ግለሰቦ ፤ለፍርድ መቅረባቸው እንዲሁም በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ሕዝቦች ብሄራዊ ክልል መንግስት በጌዲኦ ዞን መጋቢት 28, 1998  ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በከፊልም ቢሆን የመቋቋሚያ ገንዘብ በክልሉ መንግስት መሰጠቱ በጎ እርምጃ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስድ ይጠይቃል። ”

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ