የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት ይከበር!! በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚወሰድ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም!!

የህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲከበርና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ሰመጉ ጠየቀ። ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ ም ሰመጉ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መንግስት የሚያደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሐገሪቱን ወደ ከባድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ እናዳያስገባት ስጋቱን ገልጿል።

ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀመሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተባብሶ የቀጠለው ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ በርካታ ዜጐችን ለሞትና ለአካል ጉድለት ሲዳርግ፤ በሃገራችን ያለው የሰብዓዊ መብቶች አያያዝም ከመቼውም በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይም በህገ መንግስቱ የተረጋገጡትን የዜጐች የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ለመግታት በመንግስት እየተወሰደ ያለው የኃይል ርምጃ የዜጐችን ህይወት ከመቅጠፍና አካል ማጉደል አልፎ የሐገሪቱን ሰላምና ጸጥታ አስጊ ደረጃ ላይ ጥሎታል።

በተለያዩ የሐገራችን ክልሎች በተለይም በሰሜንና ደቡበ ጐንደር፤ በባህርዳር፤ በምዕራብና ምስራቅ ጐጃም የተቀጣጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ግጭት ተሸጋግሮ በርካታ ዜጐች ለሞት ተዳርገዋል። በተለይም በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 ልዩ ስሙ “ዓባይ ማዶ” አካባቢ ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ከ50 በላይ ዜጐች የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥይት ሰለባ መሆናቸውን ሰመጉ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

በተያያዘም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዳግም ያገረሸው ህዝባዊ ተቃውሞ ተስፋፍቶ በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፤ በምስራቅና በምዕራብ ሐረርጌ፤ በጅማ፤ በዝዋይ፤ በአርሲ፤ በሻሸመኔና በሌሎችም ከተሞች በመዳረስ ላይ ይገኛል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያግኙ፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*