107ኛ ልዩ መግለጫ – የብሔረሰቦች ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ያሻዋል

“የገዋዳ(አሌ) ብሔረሰብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከሚኖሩ በርካታ ብሔረሰቦች አንዱ ነው።  የብሄረሰቡ አባላት ከ1987 ዓም ጀምሮ በደራሼ ልዩ ወረዳ በሚገኙ 10 ቀ/ ገ ማህበራት ፤ በኮንሶ ልዩ ወረዳ በሚገኙ 7 ቀ ገ ማህበራት እና በደቡብ ኦሞ በሚገኙ 10 ቀ/  ገ/ ማህበራት ውስጥ ይኖራሉ።  ራሳችን ችለን በልዩ ወረዳ መደራጀት ሲገባን በተለያዩ ወረዳዎች መካከል ብሔረሰቡ ስሙን እንዲያጣ ፣  ባህልና ቋንቋውን እንዳያሳደግ  በአጠቃላይ ራሱን ከማስተዳደር ተጠቃሚ እንዳይሆን አድርጎታል በሚል የብሄረሰቡ ተወካዮች ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የክልልና የፈዴራል አካላት ሲያመለክት ቆይተዋል።

ይሁን እንጂ ይህ ልዩ በወረዳ እንካለል የሚል ጥያቄ ያቸውን አሁንም ድረስ አጥጋቢ ምላሽ እንዳለገኘ የብሄረሰቡ ተወካዮች ይናገራሉ።  በአንጻሩ ለምን እንዲህ አይነት ጥያቄ ታነሳላች ሁ በሚል የብሄርሰቡ አባላት ለእሥራት ፣ ከሥራ መባረርና ለሌሎች የበቀል እርምጃዎች ሰለባ ሆነዋል ሲሉ የብሄረሰቡ አባላት አስመልክተዋል።

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*