Latest Posts

Displacing People in the Name of Development Must Stop Immediately!

HRCO 138th Special Report (English)

In its 138th Special Report, HRCO discloses gross human rights violations committed by the Afar Regional State and Tendaho Sugar Corporation on pastoral and semi- pastoral people of Afar living in Asaita and Afambo districts.

 

በዜጐች ላይ የሚፈፀም ህገወጥ ግድያ በአስቸኳይ ይቁም!!

HRCO 139th special report ,Amharic (extrajudicial killing commited in somali regional state of Ethiopia)

በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቀላፎና ሙስታሂል ወረዳዎች የተፈፀመ የጅምላ ግድያና ድብደባን በተመለከተ ሰመጉ መግለጫ አውጥቷል:: ሰመጉ በመግለጫው ታህሳስ 1 እና 2, 2006 ዓ. ም. በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ልዩ ፖሊስ ኃይል የተገደሉ 65 ሰዎች እና ድብደባ የተፈጸመባቸው 115 ሰዎች ስም ዝርዝር አካቷል::

107ኛ ልዩ መግለጫ – የብሔረሰቦች ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ያሻዋል

“የገዋዳ(አሌ) ብሔረሰብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከሚኖሩ በርካታ ብሔረሰቦች አንዱ ነው።  የብሄረሰቡ አባላት ከ1987 ዓም ጀምሮ በደራሼ ልዩ ወረዳ በሚገኙ 10 ቀ/ ገ ማህበራት ፤ በኮንሶ ልዩ ወረዳ በሚገኙ 7 ቀ ገ ማህበራት እና በደቡብ ኦሞ በሚገኙ 10 ቀ/  ገ/ ማህበራት ውስጥ ይኖራሉ።  ራሳችን ችለን በልዩ ወረዳ መደራጀት ሲገባን በተለያዩ ወረዳዎች መካከል ብሔረሰቡ ስሙን እንዲያጣ ፣  ባህልና ቋንቋውን እንዳያሳደግ  በአጠቃላይ ራሱን ከማስተዳደር ተጠቃሚ እንዳይሆን አድርጎታል በሚል የብሄረሰቡ ተወካዮች ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የክልልና የፈዴራል አካላት ሲያመለክት ቆይተዋል።

ይሁን እንጂ ይህ ልዩ በወረዳ እንካለል የሚል ጥያቄ ያቸውን አሁንም ድረስ አጥጋቢ ምላሽ እንዳለገኘ የብሄረሰቡ ተወካዮች ይናገራሉ።  በአንጻሩ ለምን እንዲህ አይነት ጥያቄ ታነሳላች ሁ በሚል የብሄርሰቡ አባላት ለእሥራት ፣ ከሥራ መባረርና ለሌሎች የበቀል እርምጃዎች ሰለባ ሆነዋል ሲሉ የብሄረሰቡ አባላት አስመልክተዋል።

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

106ኛ ልዩ መግለጫ- ለጎሣ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ይሰጥ

“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ በዚህ 106ኛ ልዩ መግለጫው በደቡብ ብሄር ብሄረሰብ ሕዝቦች ክልል በአማሮ ኬሌ ልዩ ወረዳ በሚኖሩ የ ኮይራ ብሄረሰብ አባላትና በአዋሳኙ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አባያ ገላና ወረዳ በሚኖሩ የጉጂ ኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት መካከል በተከሰተ ግጭት የደረሰውን የሕይወት ጥፋት ፣ የንብረት ውድመትና የተለያዩ ማህበረሰባዊ ቀውሶች በቦታው በመገኘት አጣርቶ እንደሚከተለው አቅርቧል”

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

104ኛ ልዩ መግለጫ- የተማሪዎች የመሰማት መብት ይከበር

90831ba0-1
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

“ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችው የኢኮኖሚ ፣ የማኅበራዊና የባህል መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 13(1) እያንዳንዱ ሰው ትምህርት የማግኘት መብት እንዳለው ያረጋግጣል። ትምህርት የሰውን ሰብእናና ክብር በማሳደግ ለሰብአዊ መብቶች  መከበር አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባውም ይህ አንቀጽ ያሰምርበታል።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉባዔ(ኢሰመጉ) በዚህ 104ኛ ልዩ መግለጫው በማናውቀው ምክንያት ትምህርታችንን እንዳንቀጥል ተወሰነብን ሲሉ ባመለከቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የትምህርት ማስረጃ ተከለከልን ሲሉ ተመራቂ ተማሪዎች ያቀረቡትን ማመልከቻ መስረት በማድረግ ጉዳዩን አጣርቶ እንደሚከተለው አቅርቧል።”

ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

103ኛ ልዩ መግለጫ – የሕግ የበላይነት ይከበር

“የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉባኤ(ኢሰመጉ) በዚህ 103ኛ መግለጫው ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎችና በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ግንኙነት አላችሁ፤ ደጋፊዎች ናችሁ በሚልና በተለያዩ ምክን ያቶች ዜጎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደሚታሰሩ፣ ፍርድ ቤት ከቀረቡም በኋላ ቢሆን ፖሊስ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ፍርድ ቤት መዝገቡን ዘግቶ ያሰናበታቸው ፤ እንደዚሁም ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ትእዛዝ ቢሰጥም ፖሊስ ግን የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ባለማክበሩ ይህ መግለጫ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከእስር ሳይፈቱ ስለሚገኙ ዜጎች ያባሰበውን መረጃ እንደሚከተለው አቅርቧል።”

ዝርዝሩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ