105ኛ ልዩ መግለጫ- ሕጋዊ መፍ ት ሔ የሚሻ ሕገ ወጥ ድርጊት

“በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በጋሞጎፋ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በወላይታ እና በኦቾሎ ብሄረሰብ አባላት መካከል በ1992 ዓ.ም  በይዞታ ይገባኛል ሰበብ በተፈጠረ ግጭት በወላይታ ተወላጆች ላይ የሕይወት መጥፋት ፣ የንብረት መወደም  እና የወላይታ ብሄረሰብ ተወላጆች ከእድር እንደማስወጣት ያሉ የተለያዩ የማሕበራዊ ሕይወት ችግሮች ደርሰው ነበር።

ይህን ተከትሎ ከእድር እንዲወጡ የተደረጉት የወላይታ ብሄረሰብ ተወላጆች ከሌሎች ብሄረሰብ አባላት ጋር በመኾን አዲስ እድር በማቋቋም እየተረዳዱ የቆዩ ሲሆን ታህሳስ 3, 1999 ዓ.ም በላንቴ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ውስጥ በኦቾሎ ብሄረሰብ እድር ውጭ ሌላ እድር ሊኖር ስለማይገባ በአስቸኳይ እንድታፈርሱ የሚል ትእዛዝ ከላንቴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሊቀመንብር ከአቶ አለማየሁ አሻ እና ከኦቾሎ ባህል አስፈጻሚዎች ለእድሩ አመራር ኮሚቴዎች ትእዛዝ ማስተላለፉን እና ለማፍረስ ፈቃደኛ ባለመኾናቸው ምክን ያት በተለያዩ ጊዜያት የእድሩን መገልገያ እቃዎች ለመውሰድ ሙከራዎች መደረጋቸውን እና ይህንንም ህገ ወጥ ድርጊት በወቅቱ  ከወረዳ እስከ ዞን አስተዳደር ድረስ ቢያሳውቁም መፍት ሄ ሊያገኙ አልቻሉም።”
ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*