የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ)፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተር አንቀጽ 1(ሀ) እና በኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር ከ404-482 በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት መስከረም 29 ቀን 1984 ዓ.ም. በአባላት የተመሠረተ የመጀመሪያው መንግሥታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ነው፡፡ ሰመጉ በበጎ አድራጎትና ማኅበራት ዐዋጅ ቁጥር 621/2001 መሠረት “ኢትዮጵያዊ የበጎ አድራጎት ማኅበር” ሆኖ በምዝገባ ቁጥር 1146 በሕጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ሰመጉ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሃይማኖት ተቋም፣ የብሔረሰብ ቡድን፣ ማህበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ነው፡፡ ሰመጉ የቆመው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነት መስፈንና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ነው፡፡

መተዳደሪያ ደንባችንን ከዚህ በታች ይመልከቱ