Latest Posts

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የመራጮች ትምህርት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠቱን ቀጥሏል።

በባህርዳር ከተማ ለባህርዳር እና ጎንደር አሰልጣኞች ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። በቀጣይም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ይህ የመራጮች ትምህርት የአሰልጣኞች ስልጠና ይሰጣል።

ምርጫ_2013

የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) በድሬዳዋ ከተማ ለድሬዳዋ እና ጅግጅጋ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረውን የ2ቀን የመራጮች ትምህርት የአሰልጣኞች ስልጠና በስኬት አጠናቀቀ።

በቀጣይ የሰለጠኑት አሰልጣኞች በተለያዩ አካባቢዎች ለማህበረሰቡ (ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን በአጠቃላይ ተጋላጭ የማህበራችን ክፍሎችን በአካተተ መልኩ) የመራጮች ትምህርት ስልጠና የሚሰጡ ይሆናል።

Human Rights Situation in Tigray Region requires an immediate solution. በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ አስቸኳይ መፍትሔ ይሻል!

Human Rights Situation in Tigray Region requires an immediate solution.

January 22, 2021
The Ethiopian Human Rights Council- EHRCO is a non-profit, independent and impartial,
human rights organization that does not favour any political party, religious institution, ethnic
group, social class, etc., and stands to defend human rights.
Due to the conflict in the Tigray region and its environs, EHRCO is gravely concerned about the
scale of human rights abuses against unarmed civilians, conflict-prone displacement in the area, the plight of people vulnerable to suspicion and discrimination based on ethnicity, and the need
for urgent humanitarian assistance. As a result of the problem in the region, a six-month state of emergency is declared limiting the human rights of the people. Among these limitations, EHRCO has learned that people have been targeted by security forces for violating curfews. For instance, journalists Dawit Kebede and Bereket Berhe were reportedly killed by security forces on January
19, 2021. The legitimacy of such measures is highly doubtful.
EHRCO has received numerous allegations of human rights abuses, including rape, extra-judicial killings, arbitrary detention, and hostage-taking during and after the war. Women, children,
people with disabilities, and the elderly are the main victims of these abuses. In other parts of the country also, EHRCO has received numerous complaints of arrests, harassment, and discrimination against Tigrayans.
On the other hand, residents have been troubled and suffering for the past three months due to
the lack of banking services in all but a few areas, the disruption of basic services such as
electricity, water, and telephone, unpaid government workers, and poor health care facilities in numerous parts of the region….

በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ አስቸኳይ መፍትሔ ይሻል!

ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ እንዲሁም ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የኃይማኖት ተቋም፣ የብሔረሰብ ቡድን፣ ማኅበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ነው፡፡
ኢሰመጉ፤ በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት ምክንያት ባልታጠቁና ሰላማዊ በሆኑ ሰዎች ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ስፋት፣ በጦርነቱ ምክንያት ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ፣ በብሔር ማንነታቸው ብቻ ለጥርጣሬ እና መድልዎ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ሁኔታ እና አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ጉዳይ ከፍተኛ ሥጋት አሳድሮበታል፡፡ በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ችግር ምክንያት ለስድስት ወራት ያህል የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በመታወጁ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ገደቦች ተጥለዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ‹የሰዓት እላፊ ገደቦችን ጥሳችኋል› በሚል በጸጥታ ኃይሎች የኃይል እርምጃ የተወሰደባቸው ሰዎች መኖራቸውን ኢሰመጉ መረጃዎች ደርሰውታል፡፡
ለአብነት ያህል ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና በረከት በርሄ ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኢሰመጉ የእነዚህ እርምጃዎች ሕጋዊነት ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሮበታል፡፡
ኢሰመጉ በጦርነቱ ወቅት እና ከዚያም ወዲህ ባሉት ጊዜያት አስገድዶ መድፈርን፣ ከፍርድ ውጪ የሆነ ግድያን፣ ሕገ-ወጥ እስራትን እና እገታን ጨምሮ ዓይነተ-ብዙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በልዩ ልዩ አካላት እየተፈጸሙ ስለመሆኑ የሚጠቁሙ አቤቱታዎችን ተቀብሏል፣ በርካታ መረጃዎችንም አሰባስቧል፡፡ በእነዚህ የመብት ጥሰቶች ሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ቀዳሚ ሰለባዎች ስለመሆናቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌሎች የሐገሪቱ አካባቢዎችም በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ተወላጆች እስር፣ እንግልት እና መድልዎ እየደረሰባቸው ስለመሆኑም ኢሰመጉ በርካታ አቤቱታዎች ደርሰውታል…

መቆሚያ ያጣው በመተከል ያሉ ሰዎች እልቂት!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ መተከል ዞን፣ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ እጅግ አሳስቦታል፡፡ ኢሰመጉ ታህሳስ
15 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ100 በላይ ንጹኃን ሰዎች መገደላቸውን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን እና ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን
አውግዞ፤ መንግሥት በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰተውን የንጹኃን ሰዎች ሰቆቃ ለማስቆም የሚያስችል ፈጣን፣ ተጨባጭ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያበጅ ማሳሰቡ አይዘነጋም፡፡
ሆኖም፤ ከሰሞኑ ይኸው ችግር ዳግም ተከስቶ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለኢሰመጉ ተናግራዋል፡፡ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ የሚሄድ መኪና ውስጥ የነበሩ ተጓዦች ማንዱራ ከተማ ላይ በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተደርጎ አንድ ሰው መገደሉን እና ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከጥር 2 – 3 ቀን 2013 ዓ.ም በቡለን እና ጉባ ወረዳዎች፣ ኦሜድላ እና አይነሸምስ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና መኖሪያ ቤቶችም መቃጠላቸውን ኢሰመጉ መረጃዎች ደርሰውታል፡፡
በሌላ በኩል፤ ‹‹በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ትላንት ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ የኦነግ ሸኔ እና የቤኒን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን፣ እስከአሁን ድረስ እኔ ራሴ ባለሁበት የ82 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ መገኘቱን እና የቀብር ቦታዎች እየተዘጋጁ መሆኑን አይቻለሁ›› ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ ለኢሰመጉ ተናግረዋል፡፡

ኢሰመጉ፤ በትላንትናው ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሊበለጥ እንደሚችል፣ በአብዛኛው ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን እና ከ24 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቆስለው በጋሊሳ ጤና ጣቢያ እና ቡለን ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ከአካባቢው ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ ችሏል፡፡

EHRCO Preliminary Investigation Report on Major Human Rights Violations in and around Maikadra./ በማይካድራ በተፈጸመው የሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የኢሰመጉ የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ዘገባ

December 25, 2020
The Ethiopian Human Rights Council – EHRCO has been closely following the armed conflict between the Tigray regional government and the federal government since November 4, 2020. In a series of notices since the day of the conflict, EHRCO has been urging that the conflict should not endanger the safety and security of civilians and their objects.

However, during the conflict, civilians suffered a variety of physical and psychological abuses, as well as serious human rights violations, including brutal killings and sexual assaults. Of these, the November 9, 2020 massacre in Maikadra was a major one.

EHRCO sent a team of human rights investigation experts to the area to investigate the alleged human rights violations from December 3 to 11, 2020, and conducted field inspections in Makadra, Humera, Abderafi, Abrahajira, Dansha, and Gondar towns….

ታህሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም
“የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች፤ በትግራይ ክልል መንግሥት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል የነበረውን የትጥቅ ግጭት በከፍተኛ ትኩረት ሲከታተለው ነበር፡፡ ኢሰመጉ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ ቀናት ባወጣቸው ማሳሰቢያዎች ግጭቱ በምንም ዓይነት ሁኔታ ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን ደህንነትና የሲቪል ንብረቶችን አደጋ ውስጥ የሚከት እንዳይሆን ሲወተውት ቆይቷል፡፡

ሆኖም፤ በግጭቱ ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂ ግድያዎችና ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ ለልዩ ልዩ አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶች እንዲሁም ከፍተኛ ለሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ የተፈጸመው የብዙኃን ግድያ እና ወንጀል ዋነኛው ነው፡፡

ኢሰመጉ፤ ሁኔታውን ለማጣራት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያ ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥፍራው በመላክ በወቅቱ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምንነት የመለየት ሥራ ከህዳር 24 – ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በማይካድራ፣ ሁመራ፣ አብደራፊ፣ አብርሀጅራ፣ ዳንሻ እና ጎንደር ከተሞች ተዘዋውሮ የመስክ ምርመራ ሥራ አከናውኗል፡፡
የመስክ ምርመራው ግኝት የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ዘገባ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡”