በድጋሜ የወጣ ማስታወቂያ

በምርጫ መታዘብ ሥራ መሳተፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች በድጋሜ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መጭውን 6ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል። በዚሁም መረት በቀጣዩ 6ኛው አጠቃላይ ሐገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ መስፈርቶቹን የምታሟሉ አመልካቾች በ ዲጂታል አማራጮች ዎይንም በአካል በመገኘት ማመልከቻችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።

በዚህ መሠረት፡- በምርጫ ታዛቢነት የምትሰማራ/የሚሰራ ተወካይ፦

• ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላት/ያለው፣

• እድሜዋ/ው 21 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፣

• ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ የሆነች/የሆነ፤

• የመምረጥ እና የመመረጥ መብቷ/ቱ በሕግ ያልተገደበ፣

• የታወቀ ብልሹ ስነ-ምግባር የሌላት/የሌለው፣

• በእጩ ተወዳዳሪነት ያልተመዘገበች/ያልተመዘገበ፣

• ቀደም ሲል በምርጫ ታዛቢ ተወካይነት ተሰማርታ/ቶ በቦርዱ ያልታገደች/ያልታገደ መሆን አለባት/አለበት።

እንዲሁም ለምርጫ መታዘብ ሥራ በመመሪያው የወጡ ሌሎች መስፈርቶችን የምታሟሉ እና ምርጫ ለመታዘብ የምትፈልጉ ግለሰቦች ለዚሁ የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት የተጠየቁ ሰነዶችን በማያያዝ ማመልከቻችሁን በምትኖሩባቸው አካባባቢዎች (ቀጠና ጽ/ቤቶች) በአካል እንዲሁም በኢ_ሜል ቅጹን በመሙላት፣ ቃለ መሃላውን በመፈረም እና መታወቂያችሁን በማያያዝ ከታች በተቀመጡት አድራሻዎች እስከ ሰኞ ማለትም ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ እንድታስገቡ እናሳስባለን።

ዋና ጽ/ቤት፡ አዲስአበባ

አ.አ ስታዲየም አጠገብ፣ላሊበላ ሬስቶራንት ጎን፣ ሣኅለ ሥላሴ ሕንፃ 8

8ኛ ፎቅ፣ቢሮ ቁጥር 19

ኢ-ሜይል: [email protected]

ቀጠና / ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች

1. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- አዲስ አበባ ኢ_ሜል፡ [email protected]

2. ደቡብ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ሐዋሳ – ኢ_ሜል፡ [email protected]

3. ሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ባሕርዳር- ኢ_ሜል፡ [email protected]  

4. ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ነቀምቴ – ኢ_ሜል፡ [email protected]

5. ምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ድሬደዋ – ኢ_ሜል፡ [email protected]

6. ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፡- ጎንደር – ኢ_ሜል፡ [email protected]

7. ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፡- ጋምቤላ-ኢ_ሜል፡ [email protected]

8. ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፡ ጅግጅጋ-ኢሜል [email protected]  

የማመልከቻ ዝርዝር ቅጾቹን እና ቃለ መሃላውን ከስር በተያያዙት ማስፈንጠሪያዎች ወይም በዋና ጽህፈት ቤት እና የቀጠና ጽህፈት ቤቶች በግንባር መውሰድ እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ

የማመልከቻ ቅጹን ለማኘት ከታች ባለው ሊንክ ይጠቀሙ

https://ehrco-my.sharepoint.com/:w:/g/personal/info_ehrco_org/EVlgLSf1JAVGvKJUedLzihQBVC4ebFm6WlwcF4kmvqUyPQ?e=0NZC1Z

የ ታዛቢዎች ቃለ መሃላ

https://ehrco-my.sharepoint.com/:w:/g/personal/info_ehrco_org/Ec_OYm99cWhJryqSemp7HQIB6bXJ7yR5x9x5vq1dhXYamw?e=PmmfYB

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

*

*