የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መጭውን 6ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል። በዚሁም መሰረት በቀጣዩ 6ኛው አጠቃላይ ሐገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ መስፈርቶቹን የምታሟሉ አመልካቾች በ ዲጂታል አማራጮች ዎይንም በአካል በመገኘት ማመልከቻችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።
በዚህ መሠረት፡- በምርጫ ታዛቢነት የምትሰማራ/የሚሰራ ተወካይ፦
- ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላት/ያለው፣
- እድሜዋ/ው 21 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
- ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ የሆነች/የሆነ፤
- የመምረጥ እና የመመረጥ መብቷ/ቱ በሕግ ያልተገደበ፣
- የታወቀ ብልሹ ስነ-ምግባር የሌላት/የሌለው፣
- በእጩ ተወዳዳሪነት ያልተመዘገበች/ያልተመዘገበ፣
- ቀደም ሲል በምርጫ ታዛቢ ተወካይነት ተሰማርታ/ቶ በቦርዱ ያልታገደች/ያልታገደ መሆን አለባት/አለበት።
እንዲሁም ለምርጫ መታዘብ ሥራ በመመሪያው የወጡ ሌሎች መስፈርቶችን የምታሟሉ እና ምርጫ ለመታዘብ የምትፈልጉ ግለሰቦች ለዚሁ የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት የተጠየቁ ሰነዶችን በማያያዝ ማመልከቻችሁን በምትኖሩባቸው አካባባቢዎች (ቀጠና ጽ/ቤቶች) በአካል እንዲሁም በኢ_ሜል ቅጹን በመሙላት እና መታወቂያችሁን በማያያዝ ከታች በተቀመጡት አድራሻዎች እስከ ረቡዕ ማለትም ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ እንድታስገቡ እናሳስባለን።
ዋና ጽ/ቤት፡ አዲስአበባ
አ.አ ስታዲየም አጠገብ፣ላሊበላ ሬስቶራንት ጎን፣ ሣኅለ ሥላሴ ሕንፃ 8
8ኛ ፎቅ፣ቢሮ ቁጥር 19
ኢ-ሜይል: [email protected]
ቀጠና / ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች
- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- አዲስ አበባ ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ደቡብ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ሐዋሳ – ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ባሕርዳር- ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ነቀምቴ – ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀጠና፡- ድሬደዋ – ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፡- ጎንደር – ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፡- ጋምቤላ-ኢ_ሜል፡ [email protected]
- ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፡- ጅግጅጋ-ኢ_ሜል፡ [email protected]
የማመልከቻ ዝርዝር ቅጾቹን ከስር በተያያዙት ማስፈንጠሪያዎች ወይም በዋና ጽህፈት ቤት እና የቀጠና ጽህፈት ቤቶች በግንባር መውሰድ እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ
የማመልከቻ ቅጹን ለማኘት ከታች ባለው ሊንክ ይጠቀሙhttps://ehrco-my.sharepoint.com/:w:/g/personal/info_ehrco_org/EaRppHlXHPxHrogFPcgUh-8BnOIrHj1SHtMm-eP1wij3LA?e=pIGer8